የግል መረጃ
የመረጃ ጥበቃ አደራረግ ፖሊሲ
1. የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ጥቅሙ ምንድን ነው?
- በዲጂታል ግሎባል ፓስ እና በደንበኞቹ መካከል ያለውን የመተማመን ግንኙነትከግምት ውስጥ በማስገባትዲጂታል ግሎባል ፓስ የኢትዮጵያን የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2016ን እና የአውሮፓ ኅብረት የጥራት ደረጃዎች እና በተለይም በዚህ ጉዳይ ላይ ከጥቅም ላይ የሚውለውን የአውሮፓ አጠቃላይ የመረጃ ጥበቃ ደንብ (ጂዲፒአር) ከግምት ውስጥ በማስገባት የመረጃ ጥበቃ ደንቦችን በተመለከተየግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲውን ማውጣት አስፈልጓል።
- በዚህ የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የደንበኞቹን እና የደንበኞቹን ግላዊነት ለመጠበቅ በእንቅስቃሴዎቹ ማዕቀፍ እና በሥራ ላይ ባሉት ደንቦች መሠረት የተሰበሰበውን የግል መረጃ የሚደረግለትን ጥበቃ፣ ምሥጢራዊነቱን እና ደኅንነቱን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ሥራ ይሠራል።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃ ሰጪዎችን ሰብአዊ ክብር፣ ሕጋዊ ፍላጎቶች እና መሠረታዊ መብቶችን ለመጠበቅ ተስማሚ የገንዘብ፣ ሰብአዊ እና ቴክኒካዊ አመቺ መንገዶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ይሠራል።
- የዚህ የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ዋና ዓላማ በዲጂታል ግሎባል ፓስ የተከናወኑ የመረጃ አያያዝ ሥራዎችን በሚመለከት በአንድ ሰነድ ውስጥ ግልጽ፣ ቀላል እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ መረጃን ማሰባሰብ ነው። ይህም ተግባር የግል መረጃ ሰጪዎች ምን ዓይነት መረጃ እና የግል መረጃዎች (ከዚህ በኋላ «የግል መረጃዎች» በመባል የተጠቀሱት) እንደሚሰበሰቡ፣ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ እና ከእነዚህ የግል መረጃዎች ጋር በተያያዘ መብታቸው ምን እንደሆነ መረዳት እንዲችሉ ነው።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ በራሱ ምርጫ ይህንን የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ አግባብነት ባላቸው የመረጃ ጥበቃ ደንቦች መሠረት የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።
2. የግል መረጃ አስተዳደር
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ይህንን የግል መረጃ አስተዳደር ፖሊሲ አዘጋጅቷል።
- ይህ ፖሊሲ በዲጂታል ግሎባል ፓስ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መመሪያዎችን (ጋይድላይን)፣ አሠራሮችን (ፕሮሲጀር) እና ልምዶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለ ግል መረጃ አጠቃቀም ደንብ የተቀመጡትን መስፈርቶችን ያካትታል።
- በዚህ አውድ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃ ጥበቃ ኃላፊ (DPO) ይሾማል።
- የግል መረጃ ጥበቃ ኃላፊ ተግባር የመረጃ ጥበቃ ደንቦች መከበራቸውን ማረጋገጥ እና ሥልጣን ካለው ባለሥልጣን እና ከሁሉም የግል መረጃ ሰጪዎች ጋር በመተባበር የግል መረጃ አሰባሰብና ዝግጅት ላይ መልካም ግንኙነትን መፍጠር ነው።
- የግል መረጃ ጥበቃ ኃላፊውን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ሰው በሚከተለው የፖስታ አድራሻ ማግኘት ይችላል፦ «Service RGPD - 350 rue Denis Papin 13594 Aix en Provence Cedex 3» ወይም በሚከተለው ኢሜይል አድራሻ «rgpd@dgp-legal.com»።
3. ትርጓሜዎች
- «ማንነትን መደበቅ » ማለት «የግል መረጃን በማይቀለበስ መልኩ መለየትን ለመከላከል የተገኘ ውጤት» ነው፤
- «መሰብሰብ» ማለት የግል መረጃን ማግኘት ማለት ነው። መረጃ በተለይ በመጠይቆች ወይም ለመልእክቶች በሚሰጡ ምላሾች አማካይነት ሊሰበሰብ ይችላል፤
- «ስምምነት» ማለት እሱ ወይም እሷ በመግለጫ ወይም ግልጽ በሆነ አወንታዊ እርምጃ ከርሱ ወይም ከእርሷ ጋር የተያያዙ የግል መረጃዎችን እንዲሰበሰቡ ስምምነት መስጠታቸውን የሚያመለክት በነጻነት የተሰጠ፣ ልዩ በመረጃ የተደገፈ እና በማያሻማ መልኩ የመረጃ ርዕሰ-ጉዳዩን መያዝ ያስፈለገበትን ምክንያት የሚያመለክት ነው።
- «ተቆጣጣሪ» ማለት ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን የግል መረጃዎን ሂደት ዓላማዎች እና ዘዴዎችን የሚወስን ግለሰብ ወይም ሕጋዊ አካል ነው።
- «መገለጫ» ማለት «ከተፈጥሯዊ ሰው ጋር የተያያዙ አንዳንድ ግላዊ ጉዳዮችን ለመገምገም በተለይም የተፈጥሯዊ ሰውን በሥራ፣ በኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ በጤና ሁኔታ ላይ ያሉትን ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ ለመተንተን ወይም ለመተንበይ የግል መረጃን፣ የግል ምርጫዎች፣ ፍላጎቶች፣ አስተማማኝነት፣ ባህሪ፣ ቦታ ወይም እንቅስቃሴዎች የሚያካትት ማንኛውም ዓይነት በአውቶማቲክ የሚያዝ የግል መረጃ ነው፤
- «ኦንላይን አገልግሎቶች» ማለት በዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚሰጡ እንደ ድረ-ገጽ፣ መተግበሪያዎች ወይም ተዛማጅ አገልግሎቶች ያሉ ዲጂታል አገልግሎቶች ነው።
- «አቅራቢዎች» በሰፊው ሲተረጎም በተለይ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ከዲጂታል ግሎባል ፓስ ጋር የሚሠሩ ሥራ ንዑስ ተቋራጮች ማለት ነው፤
- «የግል መረጃን ማቀናበር» ማለት ከእንደዚህ ዓይነት መረጃ ጋር በተገናኘ ማንኛውም አሠራር ወይም የአሠራር ስብስብ ነው፣ ምንም ዓይነት የስብሰባ ዘዴ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤
- «ምርቶች ወይም አገልግሎቶች» በዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና አገልግሎቶች (ድረ-ገጾች፣ መተግበሪያዎች እና ተዛማጅ አገልግሎቶች) ጨምሮ ሁሉንም ምርቶች እና አገልግሎቶች ማለት ነው።
- «ደንበኛ የመሆን ተስፋ ያለው» ማለት በዲጂታል ግሎባል ፓስ ስለ ቀረበው ምርት ወይም አገልግሎት መረጃ ለማግኘት ዲጂታል ግሎባል ፓስን ያነጋገረ ማንኛውም ሰው ማለት ነው።
4. ዲጂታል ግሎባል ፓስ መቼ ነው የግል መረጃን የሚሰበስበው?
- የግል መረጃ በዋናነት በሚከተለው ዐውድ ሊሰበሰብ ይችላል፦
- ከዲጂታል ግሎባል ፓስ ጋር ግንኙነት በመፍጠር፤
- የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን (ድረ-ገጽ፣ መተግበሪያ እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ጨምሮ) በደንበኛው የሚፈጸም ማንኛውንም የዲጂታል ቪርጎ ቡድንን ምርቶች እና አገልግሎቶችን መጠቀም፤
- በዲጂታል ግሎባል ፓስ ወደፊት ደንበኛ ሊሆኑ በሚችሉ እና በደንበኞቹ መካከል በሚኖር ግንኙነት፤
- በውሎች አፈጻጸም፤
- የሕግ ወይም የቁጥጥር ግዴታዎች አፈጻጸም እና እንደ የታክስ ግዴታዎች ፣ ኦዲት ፣ ማጭበርበርን ለመዋጋት፣… ከዲጂታል ቪርጎ ቡድን እንቅስቃሴ ጋር የተዛመዱ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ፤
- እና በተለይም ቅሬታዎች በሚቀርቡበት ጊዜ ወይም የእርካታ ዳሰሳ ጥናቶች ላይ… የንግድ ግንኙነቱን ለማስተዳደር በሚደረጉ እንቅስቅሴዎች፤
5. በዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚስተናገዱ የመረጃ ምድቦች ምን ምን ናቸው?
- የግል መረጃ ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እሱን ወይም እሷን ለመለየት የሚያስችል የአንድ ተፈጥሯዊ ግለሰብን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ ነው።
- በዲጂታል ግሎባል ፓስ የተሰበሰበው መረጃ በሚከተሉት ዋና ምድቦች ሊከፋፈል ይችላል፣ የግለሰቡ መገኛ መረጃ፤ የመታወቂያ (የማንነት) መረጃ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ፎቶዎች፣ ከአገልግሎቶቹ አጠቃቀም ጋር የተገናኘ መረጃ፣ የክፍያ መረጃ።
- የግል መረጃ የአንድ ግለሰብ ስም እና የመጨረሻ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ፎቶግራፍ፣ የተቀረጸ ቪዲዮ፣ የመልእክት ልውውጦች፣ የፖስታ አድራሻ፣ የኢሜይል አድራሻ፣ የኮምፒዩተር አይፒ አድራሻ፣ ጥቅም ላይ የዋለው መሣሪያ ዓይነትን ሊያካትት ይችላል።
5.1 ገላጭ የግል መረጃ
- ገላጭ የግል መረጃዎች በግል መረጃ ሰጪዎች የሚቀርቡ እና በዲጂታል ግሎባል ፓስ የተሰበሰቡ የንግድ ወይም በውል ላይ የተመሠረቱ ግንኙነቶች ናቸው።
- መረጃው በዋነኛነት የሚገኘው ከግል መረጃ ሰጪዎች እና ወደ ዲጂታል ግሎባል ፓስ መረጃውን እንዲያስተላልፉ ከተፈቀደላቸው ከግል መረጃ ሰጪዎች ሕጋዊ ወኪሎች ነው።
- ለምሳሌ፣ የግል መረጃ ሰጪው ስለ ቤተሰቡ ሁኔታ እንዲሁም ሙሉ ስሙን እና የአድራሻ ዝርዝሮችን በተመለከተ የግል መረጃን እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል። እነዚህ መረጃዎች በኤሌክትሮኒክ ቅጾች (በድረ-ገጽ ወይም በሞባይል መተግበሪያዎች) ወይም በወረቀት ቅጾች ወይም ለምሳሌ በዲጂታል ቪርጎ ቡድን ሠራተኛ ለተጠየቁት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ መረጃዎቹ ሊሰበሰቡ ይችላሉ።
5.2 ከዲጂታል ቪርጎ ቡድን ምርቶች እና አገልግሎቶች አሠራር ጋር የተያያዘ የግል መረጃ
- የግል መረጃ በዲጂታል ቪርጎ ቡድን ምርቶች እና አገልግሎቶች የግል መረጃ ሰጪዎች አጠቃቀም ወይም በዲጂታል ግሎባል ፓስ ከግል መረጃ ሰጪው ጋር ባለው ግንኙነት ውስጥ በሚቀርቡት ምርቶች እና አገልግሎቶች በኩል ከተከናወኑ ተግባራት ጋር ሊዛመድ ይችላል።
- ለምሳሌ፣ ከደንበኞች አገልግሎት ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ወይም ከሚቀርቡት አገልግሎቶች ጋር ያለው ግንኙነት፣ ወይም ኦንላይን አገልግሎቶች አጠቃቀም (የመተግበሪያዎች አጠቃቀም) ላይ መረጃ ይሰበሰባል።
5.3 የሦስተኛ ወገኖች የግል መረጃ
- በተጨማሪም ተቀናብሮ የተሠራው (ፕሮሴስድ ዳታ) የግል መረጃ ከሚከተሉት ምንጮች ሊገኝ ይችላል፦
- ከአገልግሎት ሰጪዎች፤
- ከሕዝብ ወይም ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት፤
- የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲያቸው የሚፈቅድ ከሆነ ከንዑስ ተቋራጮች፣ ከዲጂታል ቪርጎ ቡድን አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ሦስተኛ ወገኖች
- የግል መረጃ ሰጪዎች የተመዘገቡባቸው እና/ወይም ከዲጂታል ግሎባል ፓስ ጋር መጋራት የፈቀዱ በሦስተኛ ወገኖች የቀረቡ ሌሎች ምርቶች ወይም አገልግሎቶች።
5.4 የሕዝብ የግል መረጃ
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃ ሰጪዎችን በሚመለከት ይፋዊ የግል መረጃ ሊሰበስብ ይችላል።
- የሕዝብ የግል መረጃዎች በአስተዳደር ወይም በሕዝብ ባለሥልጣን ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ወይም የሚቀበሉት በአስተዳደር ባለሥልጣን የሚታተም ወይም ማንኛውም ሰው ሲጠየቅ ሊቀርብ የሚችል የግል መረጃ ነው።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ በሕግ ወይም ደንብ በሚፈቀደው ጊዜ እና በዚህ ሕግ ወይም ደንብ የተገለጹትን ልዩ የመገናኛ እና እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ደንቦችን በማክበር የሕዝብ መረጃን ወይም የግል መረጃን ሊጠቀም ይችላል።
5.5 በዲጂታል ግሎባል ፓስ የተፈበረከ ወይም የተገመተ/የተወሰነ የግል መረጃ
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ገላጭ የሆነ የግል መረጃ ወይም ከቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አሠራር ጋር በተዛመደ መረጃ ላይ በመመሥረት አዲስ የግል መረጃን ሊያመነጭ ወይም ሊፈበርክ ይችላል።
- ይህ በተለይ ደንበኞቹን ለማወቅ፣ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን ለማስተካከል/ለማስማማት፣ ለደንበኞች ሊቀርቡ የሚችሉትን እንደ ግል ፍላጎት እንዲያገልገል ለማበጀት ይጠቅማል፣ በዚህ ጊዜ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የንግድ ወይም የግብይት መገለጫ ክፍሎችን ሊገልጽ ይችላል።
5.6 ልዩ የመረጃ ምድቦች
- ልዩ የግላዊ መረጃ ምድቦች የዘር ወይም የጎሳ አመጣጥ፣ የፖለቲካ አስተያየቶች፣ ሃይማኖታዊ ወይም ፍልስፍናዊ እምነቶች ወይም የሠራተኛ ማኅበር አባልነት፣ የግል ዘረመል መረጃ፣ የግል ባዮሜትሪክ መረጃ የተፈጥሮ ሰውን በተለየ ሁኔታ ለመለየት፣ እንዲሁም የተፈጥሮ ሰው የግብረ ሥጋ ሕይወት ወይም የግብረ ሥጋ ዝንባሌ የሚመለከት የጤና ወይም የግል መረጃዎች ናቸው።
- ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ እነዚህ ልዩ የግል መረጃ ውስጥ የሚመደቡ መረጃዎች በዲጂታል ግሎባል ፓስ አይስተናገዱም። ማስተናገድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ዲጂታል ግሎባል ፓስ ከግል መረጃ ጥበቃ ጋር በተያያዙ ደንቦች በተቀመጡት ሁኔታዎች መሠረት ለማስኬድ ይወስናል።
- የግል መረጃ ሰጪው እንደ ዘር አመጣጥ፣ ጾታዊ ዝንባሌ ወይም ሀይማኖታዊ እምነቶች የመሳሰሉ አንዳንድ መረጃዎችን ለዲጂታል ግሎባል ፓስ ለመስጠት ሊመርጥ ይችላል።
6. በዲጂታል ግሎባል የሚቀናበሩ የግል መረጃዎች ምንድናቸው?
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ከተጠቃሚው ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ዋና የግል መረጃዎችን ሊያቀናብር ይችላል፦
- የአያት ስም፣ መጠሪያ ስም፣
- ጾታ፣
- ፍለጋ የተደረገበት ጾታ፣
- ቋንቋዎች፣
- የትውልድ ቀን፦ ዕድሜ፣
- ዜግነት/ የትውልድ ቦታ፣
- የልጆች ብዛት፣
- ኢሜይል አድራሻ፣
- ፖ.ሣ. ቁጥር፦
- ስልክ ቁጥር፣
- ተለዋጭ ስም (በሞባይል ስልክ ኦፕሬተር የተመሰጠረ መለያ በአጭር የጽሑፍ መልእክት እንዲገናኝ በመፍቀድ)፤
- ተዛማጅ ከሆኑ ሰዎች (ልጆች፣ ወላጆች፣ ባለትዳሮች) ጋር የተያያዘ መረጃ፤
- ለመገናኛ እና ለኤክትሮኒክስ መተግበሪያዎ የተሰጠ ምክር መረጃ (አይፒ፣ መሣሪያ፣ የድረ ገጽ ምልከታ፤ ዱካ /ፈለግ መከታተያዎች)፤
- ፎቶዎች፤
- በማኅበረሰብ አገልግሎቶች ወይም ከደንበኞች አገልግሎት ጋር በተገናኘ የሚለዋወጧቸው መልእክቶች፤
- የላኳቸው ወይም የተቀበሏቸው አጭር የጽሑፍ መልእክት፤
- ከደንበኞች አገልግሎት ጋር የሚደረግ ውይይት፤
- እሴት ወደተጨመረባቸው አገልግሎቶች የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች፤
- የደንበኛው የባንክ መረጃ ዝርዝር / አርአይቢ፤
- መታወቂያ ወረቀት፣
- የስልክ ክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ፣
7. በዲጂታል ግሎባል ፓስ የተሰበሰበው መረጃ ተቀባዮች እነማን ናቸው?
7.1 ዲጂታል ግሎባል ፓስ እንደ መረጃ ተቆጣጣሪ ሆኖ ሲሠራ
- የተሰበሰቡት ግላዊ መረጃዎች እና በኋላ ላይ የሚገኙት ለዲጂታል ግሎባል ፓስ እንደ መረጃ መቆጣጠሪያ አቅሙ የታሰቡ ናቸው።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃ ሰጪዎች ግላዊ መረጃ በተፈቀደላቸው ሰዎች ብቻ እና ለሥራቸው አፈጻጸም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ መረጃውን ማግኘት መቻላቸውን ያረጋግጣል።
- አንዳንድ የግል መረጃዎችበሕግ፤ በደንብ ወይም በውል የተጣሉትን ግዴታዎችን ለማክበር እንዲሁም በሕጋዊ መንገድ ለተፈቀደላቸው አካላት ምላሽ ለመስጠት ሲባል ለሦስተኛ ወገኖች ሊላኩ ይችላሉ።
- የመረጃ ተቀባዮች ምድቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ ደንበኞች፣ ዲጂታል ቪርጎ ቡድን ኩባንያዎች፣ የገንዘብ እና የሒሳብ ክፍሎች፣ የሕግ ክፍል፣ የሽያጭ ክፍል፣ የውስጥ ደንበኞች ግንኙነት አገልግሎት፣ የቴክኒክ አቅራቢዎች፣ የደንበኛ ግንኙነት ኃላፊነት አገልግሎት አቅራቢዎች.
7.2 ዲጂታል ግሎባል ፓስ እንደ መረጃ አቀናባሪ ሆኖ ሲሠራ
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ከአጋሮቹ ጋር በገባው ውል መሠረት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የተሰበሰበውን መረጃ ተቆጣጣሪ እና የመጨረሻ ተቀባይ ሆነው የሚሠሩ አጋሮቹን ወክሎ መረጃን ሊሰበስብ እና
ሊሠራ ሊያቀናብር ይችላል።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ዲጂታል ግሎባል ፓስ ተቆጣጣሪ በሆነባቸው ተመሳሳይ ሂደቶች እና መረጃዎች ላይ ተመሳሳይ የደኅንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ያረጋግጣል።
8. ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃውን ለምን ያህል ጊዜ ይዞ ያቆያል?
- የግል መረጃ በዲጂታል ግሎባል ፓስ የመረጃ ሥርዓቶች ወይም በንዑስ ተቋራጮች/በንኡስ ተዋዋዮች ወይም አቅራቢዎች ውስጥ ይከማቻል። ለሦስተኛ ወገኖች የሚተላለፍ ከሆነ፣ የግል መረጃዎች በመረጃ ማእከል ውስጥ ተከማችተው በአውሮፓ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ።
- በመርህ ደረጃ፣ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የጥራት እና የደኅንነት መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ንዑስ ተቋራጮችን እና አቅራቢዎችን ለመምረጥ እና ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን ለመተግበር በአስተማማኝ፣ በደኅንነት እና በንብረቶች ላይ በቂ ዋስትናዎችን እንዲሰጡት ያስደርጋል።
- በመጨረሻም፤ ዲጂታል ግሎባል ፓስ ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ለሕግ ተገዢ መሆኑን ለማረጋገጥ መረጃው የሚስተናግድበትን (የሚቀመጥበትን) ቦታ በማንኛውም ጊዜ ያሳውቃል።
9. የግል መረጃን ለመጠበቅ የሚረዱ መመሪያዎች
- ጂዲፒአር ግላዊ መረጃቸው ለሚሰጡ ግለሰቦች መረጃ የመስጠት ግዴታን ይበልጥ የተጠናከረ እንዲሆን አድርጓል።
9.1 ሕጋዊነት፣ ፍትሐዊነት እና ግልጽነት
9.1.1 ሕጋዊነት
- ሕጋዊነት የሚመዘነው ከዚህ በታች በተገለጹት ሁኔታዎች ከመሆኑ አንፃር ይህንንኑ በመረዳት ዲጂታል ግሎባል ፓስ መረጃን በሕገ-ወጥ መንገድ አያስተናግድም (አይጠቀምም)።
- የመረጃ ርዕሰ ጉዳይ ስምምነት፤ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃ ሰጪው የግል መረጃውን ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓላማዎች መረጃውን ለማቀናበር ፈቃድ ከሰጠ የመረጃ ማቀናበርን ሊያከናውን ይችላል።
ለአካለ መጠን ያልደረሱ። በዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለአካለ መጠን ላልደረሱ ሕፃናት እንዲያገለግሉ የታሰቡ አይደሉም። የግል መረጃ ሰጪው የዲጂታል ግሎባል ፓስ አገልግሎቶችን ለመመዝገብ ወይም ለመጠቀም ዕድሜው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆኑን ያረጋግጣል። ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጃቸው አገልግሎቶቹን መጠቀም ይፈቀድለት እንደሆነ የመወሰን የወላጆች እና የሞግዚትነት ሥልጣን ያለው ማንኛውም ሰው መብት ነው።
- እንዲህ ዓይነቱ ስምምነት በኤሌክትሮኒክ መንገድ፣ ወይም የቃል መግለጫ፣ ወይም አገልግሎቶቹን በሚጠቀሙበት ጊዜ በጽሑፍ መግለጫ ሊሰጥ ይችላል።
- ውሉ ከመግባቱ በፊት የውሉ አፈጻጸም ወይም እርምጃዎችን መውሰድ ዲጂታል ግሎባል ፓስ ለውሉ አፈጻጸም ሂደት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መረጃውን ሊያስተናግድ (ሊሰበስብ) ይችላል።
- ለምሳሌ፣ ማቀናበር የሚተገበረው በውሉ አፈጻጸም ማዕቀፍ ውስጥ ሲሆን ለምሳሌ ከክፍያ ክፍያዎች ወይም ያልተከፈለ ደረሰኞች አስተዳደር ውሎችን ሲይዝ እና ሲመራ።
- የሕግ እና የቁጥጥር ግዴታዎች። ዲጂታል ግሎባል ፓስ ሕጋዊ ወይም የቁጥጥር ግዴታዎችን ለማክበር ሂደት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መረጃውን ሊያስተናግድ (ሊሰበስብ) ይችላል።
- እነዚህ የሕግ ወይም የቁጥጥር ግዴታዎች ለምሳሌ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚገዛበትን የውስጥ ቁጥጥር እና በተለይም የባንክ እና የታክስ ግዴታዎችን በተመለከተ ከቁጥጥር እና ከቁጥጥር ጋር የተያያዙትን ያካትታሉ። ዲጂታል ግሎባል ፓስ ለውሉ አፈጻጸም ሂደት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መረጃውን ሊያስተናግድ (ሊሰበስብ) ይችላል።
- በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ በሕግ ወይም ደንብ ከተፈለገ የተወሰኑ ሥራዎችን የሚመለከቱ ልዩ መረጃዎችን መጠየቅ እና የግል መረጃዎችን እና መረጃዎችን ለሦስተኛ ወገኖች ማስተላለፍ ሊያስፈልግ ይችላል።
- የዲጂታል ቪርጎ ቡድን ሕጋዊ ፍላጎቶች። ዲጂታል ግሎባል ፓስ በዲጂታል ቪርጎ ቡድን ወይም በሦስተኛ ወገን ለሚከተሏቸው ሕጋዊ ፍላጎቶች ዓላማዎች ሂደት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መረጃውን ሊያስተናግድ (ሊሰበስብ) ይችላል።
- በዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚከተሏቸው ሕጋዊ ፍላጎቶች የተለያዩ ናቸው ነገርግን በተለይ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦
- የግል መረጃ ሰጪዎችን የግብይት ዕውቀት ማሻሻል፤
- የምርት እና አገልግሎቶች መሻሻል፤
- ክፍፍል፣ መገለጫ፣ ቀጥተኛ ግብይት፣ የግብይት ክፍፍል.
- እንደነዚህ ያሉ የማቀናበር ሥራዎች የሚከናወኑት የግል መረጃ ሰጪዎችን ፍላጎቶች እና መሠረታዊ መብቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ስለሆነም የግል መረጃ ሰጪዎችን ፍላጎቶች እና መብቶች ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ እና በዲጂታል ግሎባል ፓስ ውስጥ የሚኖሯቸውን ሕጋዊ ፍላጎቶች ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለመጠበቅ ከሚወሰዱ እርምጃዎች እና ከሚኖሯቸው ዋስትናዎች ጋር አንድ ላይ ተጣምረው ቀርበዋል።
9.1.2 ፍትሐዊነት እና ግልጽነት
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ግልጽ መረጃን ለማቅረብ ይሠራል።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ በመረጃ ማሳወቂያዎች አማካኝነት የሚያከናውናቸውን እያንዳንዱንየመረጃ ማቀናበር ሥራዎች የዳታ ባለቤት በማሳወቅ ይሠራል።
9.2 የተለዩ፤ ግልጽ እና ሕጋዊ ዓላማዎች
- በዲጂታል ግሎባል ፓስ የተሰበሰበ ግላዊ መረጃ የሚሠራው ለተወሰኑ፣ ግልጽ እና ሕጋዊ ዓላማዎች በማንኛውም ጊዜ ነው።
- የደንበኞቹን የግል መረጃ ሥነምግባር እና ደኅንነት ለመጠበቅ ቁርጠኛ የሆነው ዲጂታል ግሎባል ፓስ በዚህ የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ውል መሠረት የግል መረጃን ይጠቀማል።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃውን በሙሉ ወይም በከፊል ለሚከተሉት ዋና ዓላማዎች ይጠቀማል።
- ውል ከመግባቱ በፊት በግል መረጃ ሰጪዎች ጥያቄ መሠረት እርምጃዎችን መውሰድ፤
- ከደንበኞቹ ጋር ውሎችን እና ግንኙነቶችን ማስተዳደር፤
- ከዲጂታል ቪርጎ ቡድን አጋሮች ጋር በተላኩ ቅሬታዎች ወይም ጥያቄዎች ውስጥ የመልእክት ልውውጥን ማስተዳደር፤
- ተግባራቶቹን ማስተዳደር (ለምሳሌ የውስጥ እና የውጭ ኦዲት) እና የሕግ ግዴታዎችን ማክበር፤
- መሣሪያዎችን፣ ድረ-ገጽዎችን እና መተግበሪያዎችን ማስተዳደር፣ እና መጠበቅ፤
- ጥራትን እና እርካታን መለካት፤
- የሚሰጡትን አገልግሎቶች ማሻሻል፤
- የአገልግሎት ፈጠራን ማዳበር፤
- የማመልከቻ ሥራዎችን ማከናወን፤
- የንግድ ስታቲስቲክስ ማዘጋጀት፤
- ከመብታቸው ጋር በተያያዘ የመረጃ ርዕሰ ጉዳይ ጥያቄዎችን ማስተዳደር፤
- ያልተከፈሉ ዕዳዎችን፣ ሙግት፣ ማታለል ድርጊቶችን፣ የገንዘብ ማጭበርበርን እና የአሸባሪዎች የገንዘብ ድጋፍ መስጠትን እና የታክስ ስወራን መከላከል እና መቆጣጠር፤
- በምርቶች ፣ አገልግሎቶች ወይም ይዘቶች ላይ የሰዎችን አስተያየት ማስተዳደር፤
- ስለ ደንበኛው ዕውቀት ማግኘት።
9.3 በቂነት፣ ተገቢነት እና ገደብ
- ለእያንዳንዱ የማቀነባበሪያ ክዋኔ፣ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የማቀነባበሪያ ሥራዎች በቂ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እና ለተከተለው ዓላማ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ብቻ ለመሰብሰብ እና መረጃ ለማቀናበር ይሠራል።
9.4 የመረጃ ትክክለኛነት
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ የሚሰበሰበው መረጃ የተሟላ እና ሁኔታ በሚፈቅደው መጠን የተዘመነ መሆኑን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው።
- የግል መረጃባለቤቶች ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ መኖሩን ካወቁ፣ ከዚህ በታች በተገለጹት ሁኔታዎች መሰረት የማረም መብታቸውን የመጠቀም መብት አላቸው.
9.5 የማከማቻ ጊዜ እና ገደብ
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃን የተከማቸበትን ዓላማ ለመፈጸም ከሚያስፈልገው በላይ ወይም ከግል መረጃ ጥበቃ ጋር በተያያዙ ደንቦች ከተደነገገው ጊዜ በላይ እንደማይይዝ ያረጋግጣል።
ቁጥር | የግል መረጃ ምድቦች | በንቃት ጠብቆ የማቆየት መርሆዎች |
1. | የደንበኛ እና ደንበኛ ለመሆን ተስፋ ያላቸው ፋይል አስተዳደር | ለደንበኞች፡ ለኮንትራት ግንኙነቱ ጊዜ እና ከዚያ በኋላ ባሉት 5 ዓመታት ደንበኛ ለመሆን ተስፋ ላላቸው፦ ከደንበኛ ለመሆን ተስፋ ካለው ግለሰብ የመጨረሻ ግንኙነት 3 ዓመታት |
2. | የትንታኔ ስታትስቲክስ | 13 ወራት |
3. | የውስጥ ጋዜጣ አስተዳደር | እስከ ደንበኝነት ምዝገባ ድረስ |
4. | ፎቶዎች | እስኪሰረዝ ድረስ ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ ከወጡ 6 ወራት በኋላ ወይም ከመጨረሻው የአገልግሎት መዳረሻ 3 ዓመታት በኋላ |
5. | መልእክቶች ወይም ቅጂዎች | 1 ዓመት |
- የማቆያ ጊዜው ካለቀ በኋላ መረጃው ከዲጂታል ግሎባል ፓስ የመረጃ ሥርዓት ይሰረዛል።
9.6 ለደኅንነት እና ምሥጢራዊነት ያለ ቁርጠኝነት
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ከማናቸውም ተንኮል-አዘል ጣልቃገብነት፣ መጥፋት፣ ለውጥ የማድረግ ወይም ላልተፈቀደ የሦስተኛ ወገኖች እንዳይገለጽ ለመከላከል ለግል መረጃው የትብነት ደረጃ ተስማሚ የሆኑ የደኅንነት እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም አለው።
- ሁሉም የዲጂታል ግሎባል ፓስ ህንጻዎች የግል መረጃዎች የሚስተናገዱባቸው ቦታዎች ከኤሌክትሮኒካዊ እና/ወይም በማኑዋል ካልተፈቀዱ የሦስተኛ ወገኖች ጣልቃ ገብነት ጥበቃ ይደረግላቸዋል።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ በንድፍ እና በቅድሚያ አሠራር የግል መረጃ ጥበቃ መርሆዎችን የሚያከብሩ የውስጥ ፖሊሲዎችን እና ሂደቶችን ተግባራዊ ያደርጋል።
- ለምሳሌ ይህ በተቻለ መጠን ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የግል መረጃን የውሸት ስም መስጠትን ሊተገበር ይችላል።
9.7 የግል መረጃ ባለቤቶች መብቶች
- ከዲጂታል ግሎባል ፓስ በሕጋዊ መንገድ ካልተፈለገ በስተቀር መረጃቸው የተሰበሰበባቸው ግለሰቦች የሚከተሉት መብቶች ይኖሯቸዋል፦
- የመረጃ መብት፤
- መረጃውን የማግኘት መብት፤
- መረጃውን የማረም መብት፤
- መረጃውን የመደምሰስ ወይም የመረሳት መብት፤
- መረጃውን የማንቀሳቀስ መብት፤
- መረጃውን የመቃወም መብት፤
- የመረጃውን ማቀነባበሪያ ሂደትን የመገደብ መብት፤
- መረጃውን የመጠየቅ መብት፤
- ከሞቱ በኋላ የግል መረጃን ለማከማቸት፣ ለማጥፋት እና ለማስተላለፍ ትእዛዞችን የመስጠት መብት።
9.7.1 እነዚህን መብቶች የመተግበር ሂደቶች
- በዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃን ለማቀናበር ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት እባክዎ በሚከተለው አድራሻ ያነጋግሩ፦ rgpd@dgp-legal.com
9.7.2 ቅሬታ የማቅረብ መብት
- የግል መረጃ ባለቤቶች ለማንኛውም ሌላ የአስተዳደር ወይም የፍትሕ መፍትሔ ሰጪ አካል ያለምንም ገደብ ቅሬታቸውን ለተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የማቅረብ መብት አላቸው።
- የግል መረጃ ባለቤቶች ይግባኛቸውን ለተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ሊያቀርቡ ይችላሉ።
9.8 አውቶማቲክ ውሳኔ አሰጣጥ
- የግል መረጃ ሰጪዎች የግል መረጃቸውን ለአውቶሜትድ ሂደት፣ ለመገለጫ ዓላማዎችም ጭምር መጠቀም እንደሚችሉ ይነገራቸዋል።
- «መገለጫ» ማለት «ከተፈጥሮ ሰው ጋር የተያያዙ አንዳንድ ግላዊ ጉዳዮችን ለመገምገም በተለይም የተፈጥሮ ሰውን በሥራ፣ በኢኮኖሚ፣ በጤና ሁኔታ የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለመተንተን ወይም ለመተንበይ የሚያካትተው ማንኛውም ዓይነት የግል መረጃን በአውቶማቲክ የማዘጋጀት ዘዴ ነው። ፣ የግል ምርጫዎች፣ ፍላጎቶች፣ አስተማማኝነት፣ ባህሪ፣ ቦታ ወይም እንቅስቃሴዎች» ናቸው።
- የግል መረጃ ሰጪዎች ፕሮፋይል ማድረግን ጨምሮ እንዲህ ያለው ውሳኔ በእነሱ ላይ ሕጋዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር ከሆነ ወይም በተመሳሳይ ሌላ መልኩ በእነርሱ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድርባቸው ከሆነ በአውቶማቲክ ሂደት ላይ ብቻ የተመሠረተ ውሳኔ ተገዢ ያለመሆን መብት አላቸው። ውሳኔው በግል መረጃ ሰጪ እና በዲጂታል ግሎባል ፓስ መካከል ያለውን ውል ወይም ለመፈጸም አስፈላጊ ከሆነ ወይም በግል መረጃ ሰጪው ግልጽ ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ከሆነ ይህ መብት ተፈጻሚ አይሆንም።
- ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ውስጥ የተከናወኑ የግል መረጃዎችን በአውቶማቲክ ማካሄድ በዲጂታል ግሎባል ፓስ ለግል መረጃ ሰጪ መብቶችን እና ነጻነቶችን እና ሕጋዊ ፍላጎቶችን ለመጠበቅ ተስማሚ የሆኑ እርምጃዎች ብቻ መወሰድ አለባቸው።
- በተጨማሪም የግል መረጃ ሰጪዎች የሰውን ጣልቃ ገብነት የመጠየቅ ወይም አመለካከታቸውን የመግለጽ ወይም የተወሰደውን አውቶማቲክ ውሳኔ የመቃወም መብት አላቸው።
9.9 መገለጫ /ማጠናቀር
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን ለማሻሻል እና ከዲጂታል ግሎባል ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ቅናሾችን ለመላክ የግል መረጃን በተለይም የግል መገኛ መረጃን እንዲሁም ለንግድ እና ለማስታወቂያ ዓላማዎች የሚተላለፉ ሌሎች መረጃዎችንለማስተላለፍ እንደ አጭር የጽሑፍ መልእክት (ኤስ.ኤም.ኤስ)፣ ጋዜጣ እና ሌሎች የማስታወቂያ መልእክቶች ያሉ የፓስ ምርቶች እና አገልግሎቶች ለመረጃ ጉዳዮች ሊጠቀም ይችላል።
- ለእንደዚህ ዓይነቱ ሂደት የግል መረጃ ሰጪዎች ፈቃድ ሁል ጊዜ ያስፈልጋል።
9.10 ከአውሮፓ ኅብረት ውጭ ለሚደረጉ ዝውውሮች የሚመለከት ማዕቀፍ
- የአውሮፓ ዜጎች በመስማማት ወደ ዲጂታል ግሎባል ፓስ ያስተላለፉት የግል መረጃቸው በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ ወይም ከአውሮፓ ኅብረት ውጭ ወደሚገኝ ሀገር ይተላለፋል።
- ከአውሮፓ ኅብረት ውጭ ወደሚገኝ ሀገር የሚዛወሩ ከሆነ የመረጃውን ጥበቃ እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ሕጎች ይዘረጋሉ።
- በሁሉም ሁኔታዎች ዲጂታል ግሎባል ፓስ የግል መረጃን ደኅንነት ለማረጋገጥ ሁሉንም አስፈላጊ እና ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳል።
- እነዚህ የግል መረጃዎች በግል መረጃ ሰጪዎች ጥያቄ፣ ለባለሥልጣናት እና ለተፈቀደላቸው የአስተዳደር ወይም የፍትሕ አካላት ወይም ለሦስተኛ ወገኖች ሊተላለፉ ይችላሉ።
10. ልዩ የመረጃ ማቀናበር ሂደት
10.1 ኩኪዎች እና ሌሎች የመከታተያ ቴክኖሎጂዎች
- ስለ ኩኪዎች ወይም ስለሌሎች የመከታተያ ቴክኖሎጂዎች ስንናገር፣ የተቀመጡትን መረጃዎች የሚያነቡ ቴክኖሎጂዎች ማለት ነው። ለምሳሌ ድረ-ገጽን ሲያማክሩ፣ ኢሜይል ሲያነቡ፣ ሲጭኑ ወይም ሲጠቀሙ ሶፍትዌር ወይም የሞባይል መተግበሪያ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ምንም ይሁን ምን የሚገኘው መረጃ ማለት ነው።
- የድረ-ገጾቹን አጠቃቀም እና ተግባራዊነት ለማሻሻል ዲጂታል ግሎባል ፓስ የተለያዩ ዓይነት ኩኪዎችን ወይም እንደ ፒክስል ታግ ያሉ ሌሎች መከታተያዎችን ይጠቀማል፣ አንዳንዶቹም በአውቶማቲክ ቅጂ የግል መረጃዎችን ወደ ዲጂታል ግሎባል ፓስ ድረ-ገጾች ሊያስተላልፉ ይችላሉ።
- ዲጂታል ግሎባል ፓስ ለድረ-ገጽዎቹ የኩኪ ፖሊሲ አዘጋጅቷል። ለበለጠ መረጃ እባክዎ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት በድረ ገጹ ላይ የሚገኘውን የኩኪ ፖሊሲ ይመልከቱት።
10.2 ፕላግ-ኢን እና ማኅበራዊ ሞጁሎች
- የዲጂታል ግሎባል ፓስን ድረ-ገጾች ወይም መተግበሪያዎችን በመረጃ ርዕሰ ጉዳዮች ማግኘት እና መጠቀም የሦስተኛ ወገን አገልግሎት አቅራቢዎችን የግል መረጃን ሊሰጥ ይችላል።
- እነዚህ ባህሪያት በራሳቸው ስለማይሠሩ/ስለማይነቁ የተጠቃሚዎችን ግልጽ ፍቃድ ይፈልጋሉ። ለምሳሌ፣ ተጠቃሚው የተወሰኑ ባህሪያትን ከተጠቀመ፣ የዲጂታል ግሎባል ፓስ ድረ-ገጾች ግላዊ መረጃዎችን እንደ ፌስቡክ፣ ቲውተር ወይም ኢንስታግራም ለመሳሰሉ ማኅበራዊ ትስስር አውታረ መረቦች ሊገናኙ እና ሊያስተላልፉ ይችላሉ።
- እነዚህ ማኅበራዊ አውታረ መረቦች የእርስዎን መረጃ ለሌሎች ነገሮች ለክትትልና ለማስታወቂያ ዓላማ ስለሚጠቀሙ፣ ዲጂታል ግሎባል ፓስ የእነዚያን አውታረ መረቦች የመረጃ ፖሊሲዎች እንዲያማክሩ እና የመረጃዎን ምሥጢራዊነት ለመጨመር እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይመክራል።