ኩኪዎች

ዲጂታል ግሎባል ፓስ

መረጃ ሰጪ ኩኪዎች

አሰሳ በሚያደርጉበት ወቅት የእኛ ድረገጽ ከኮምፒዩተርዎ፣ ከሞባይልዎ ወይም ከታብሌትዎ አሳሽ ላይ በኩኪዎች አማካይነት መረጃ ሊሰበስብ ወይም ሊያከማች ይችላል።

ድረ ገጻችን የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማሟላት እና ለደንበኞች የሚጠብቁትን አገልግሎት ደረጃውን ጠብቆ ለማቅረብ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የደንበኞቻችንን ፍላጎትና ምርጫ በተሻለ መንገድ ለማሟላት እንድንችል ኩኪዎችን የምንጠቀምባቸው የተለያዩ ዓይነት መንገዶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

ለምሳሌ እርስዎ ማን እንደሆኑ ለይቶ ማወቅ እና ወደ መለያዎ እንዲደርሱበት ለእርስዎ ፈቃድ መስጠት፣ የሚያደርጓቸውን ውይይቶች መዝግቦ ማስቀመጥ፣ የምናቀርባቸውን ልዩ አገልግሎቶች በእርስዎ ፍላጎት ላይ ተመርኩዞ ማስተካከል እና የእኛንን ትራፊክ መርምሮ ትንታኔ መስጠት

ይህ መረጃ ስለእርስዎ፣ ስለ ምርጫዎችዎ ወይም ስለ መሣሪያዎ የተመለከተ መረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ በዋንኛነት ድረ ገጻችን እርስዎ በሚጠብቁት ደረጃ ያለምንም እንከን እንዲሠራ ለማድረግ ያገለግላል።

እንዲሁም ስለ ድረ ገጻችን አጠቃቀምን በተመለከተ ከማኅበራዊ ትስስር መድረኮች፣ ከማስታወቂያ እና ከትንታኔ አጋሮቻችን ጋር መረጃን የምንጋራው ይሆናል። መረጃውም የእርስዎን ማንነት በቀጥታ ለይቶ ሳያውቅ እርስዎ የበለጠ ግላዊነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ ተሞክሮ እንዲኖርዎት ሊያደርግዎት ይችላል። ይህ መረጃ በእርስዎ ኮምፒዩተር ውስጥ ተይዞ የሚቆይበት የጊዜ መጠን እርስዎ በሚጎበኙዋቸው ድረገጾች ላይ የሚመሰረት ይሆናል።

ኩኪዎች እና ዱካ ጠቋሚዎች ለምን ዓላማ ጥቅም ላይ ይውላሉ?

በኛ ድረ ገጽ ላይ የተለያየ ጥቅም ያላቸው የተለያዩ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። አንዳንዶቹ ኩኪዎች የእኛን ድረ ገጽ ለመጠቀም የግድ አስፈላጊ ናቸው።

የእርስዎን ግላዊነት መብት የምናከብር እንደመሆኑ የተወሰኑ ዓይነት ኩኪዎችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የመከልከል አማራጭ አልዎት። ይሁን እንጂ የተወሰኑ ዓይነት ወሳኝነት ያላቸው ኩኪዎችን ካገዱብን በእኛ ጣቢያ ላይ የሚኖርዎት ተሞክሮ ላይ እና እንዲሁም እኛ ልንሰጥዎት በምንችለው አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጠር ያደርጋል።

በጣም አስፈላጊ ኩኪዎች

እነዚህ ኩኪዎች የእኛን ድረ ገጽ በትክክል ሥራውን እንዲሠራ የግድ አስፈላጊዎች ናቸው። የድረ ገጻችንን ዋንኛ ባሕሪያት (ለምሳሌ ወደ የእርስዎ መለያ መድረስ የመሳሰሉትን) እርስዎ መጠቀም እንዲችሉ ያደርግዎታል። ያለ እነዚህ ኩኪዎች የእኛን ድረ ገጽ በተለመደው መንገድ ሊጠቀሙበት አይችሉም። እነዚህ ኩኪዎች በኛ ድረገጽ የሚለጠፉ ሲሆኑ ዋንኛ ዓላማቸውም የኛ ድረገጽ በአግባቡ መሥራቱን ማረጋገጥ ብቻ ነው።

እነዚህን ኩኪዎች እንዲያግድ ወይም ጥቅም ላይ ሲውሉ እርስዎን እንዲያስጠነቅቅዎት አድርገው የእርስዎን አሳሽ ማስተካከል ይችላሉ ነገር ግን የድረ ገጹ አንዳንድ ክፍሎች በዚህ ምክንያት በአግባቡ ላይሠሩ ይችላሉ። እነዚህ ኩኪዎች ምንም ዓይነት በግል ማንነትን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል መረጃን አያከማቹም።

የምናስቀምጣቸው ኩኪዎች ምሳሌዎች፦

PHPSESSID ወይም nautisession_v3፦ መረጃ ሳይጠፋ ከአንድ ገጽ ወደ ሌላኛው መሸጋጋር የሚያስችል የአሰሳ ማድረጊያ ውሂብን (መረጃን) ለማስቀመጥ የሚጠቅም ኩኪ ነው፡፡

SB_CNIL፦ ተጠቃሚው ኩኪዎችን በተመለከተ የቀረበለትን መረጃ ሲቀበል እና እንደገና ኩኪዎቹን እንዲቀበል ጥያቄ እንዳይቀርብለት ለማድረግ የሚቀመጥ ኩኪ ነው፡፡

authkey፦ ተጠቃሚው ፈቃድ ሲያገኝ የሚቀመጥ ኩኪ። ተጠቃሚው እንደገና የመለያ መግቢያ እና የይለፍ ቃል ደጋግሞ ማስገባት ሳይኖርበት በድጋሜ ፈቃድ እንዲያገኝ የሚያስችለው ኩኪ ነው፡፡

ሪዞሊዩሽን፦ የተጠቃሚውን ማያ ገጽ (ስክሪን) የቀለም ውሁድ እና እፍገት በማወቅ ማያ ገጹን ለተሻለ አጠቃቀም ተስማሚ እንዲሆን አድርጎ ለማስተካከል የሚቀመጥ ኩኪ።

SB_ADBLOCKDETECT፦ ተጠቃሚ ማስታወቂያ ማገጃ እንዳለው የሚጠቁም መልእክትን ሲመለከት የሚቀመጥ ኩኪ

የትንታኔ መስጫ ኩኪዎች

እነዚህ የእኛ ድረ ገጽ አጠቃቀም እና ሥራ አፈጻጸም ለማወቅ እና የሥራ ክንውኑን ማሻሻል እንድንችል የሚያደርጉን (ለምሳሌ በድረ ገጻችን ውስጥ የትኛው ገጽ ይበልጥ እንደሚጎበኝ ለማወቅ የሚረዱን) ኩኪዎች ናቸው።

በኩኪ የሚሰበሰበው ሁሉም መረጃ አንድ ላይ ስለሚጠራቀም የማን እንደሆነ ለማወቅ አያስችልም። እነዚህ ኩኪዎች ካልተዋቸው እርስዎ የኛን ጣቢያ እንደጎበኙ ማወቅ ስለማንችል የጣቢያውን የአፈጻጸም ብቃት መቆጣጠር አንችልም። እነዚህ ኩኪዎች በዋንኛነት በእኛ ድረገጽ የሚቀመጡናቸው።

የምናስቀምጣቸው ኩኪዎች ምሳሌዎች፦

_ga: ልዩ ኩኪን ለመመደብ እና የተጠቃሚን ፅንሰ ሐሰብ ለማብራራት በ Google Analytics ጥቅም ላይ የሚውል።

_GID: በ Google Analytics ጥቅም ላይ የሚውል የድረ ገጽ አጠቃቀም ስታትስቲክስን ለማመንጨት የሚመደብ ልዩ ቁጥር ነው።

_gat: የጥያቄ ድግምግሞሽን በእጅጉ ለመቀነስ በ Google Analytics ጥቅም ላይ የሚውል ነው።

_dc_gtm_: የጥያቄ ፍጥነትን ለመገደብ በGoogle Tag Manager ጥቅም ላይ የሚውል - ከፍተኛ ትራፊክ ባለባቸው ጣቢያዎች ላይ ውሂብን ለመገደብ ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡

_gcl_au: ከተለያዩ የቀጥታ ወይም ከተጠቀሱ የማስታወቂያ ድረ ገጾች ንግግሮችን ለመከታተል በGoogle Ads ጥቅም ላይ ይውላል

ተግባራዊ ኩኪዎች

እነዚህ በድረ ገጻችን ላይ ያለዎትን ልምድ ለእርስዎ በልዩ መልክ ለግልዎ እንደሚመች አድርገን እንድናዘጋጅ የሚፈቅዱ ኩኪዎች ናቸው። እንዲሁም እንደ አመጣጥዎ የኋላ የዳሰሳ ታሪክ (ለምሳሌ ከኛ አጋር ድረ ገጾች የመጡ ከሆኑ) ከኛ ግላዊ ምክር እና ልዩ የማስተዋወቂያ ቅናሾችን በማግኘት እርስዎን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችሉዎታል። እንዲሁም እርስዎ የጠየቁዋቸውን ባሕሪያት እኛ ማቅረብ እንድንችል ሊያገለግሉን ይችላሉ።

የማስታወቂያ ክትትል ማድረጊያ ኩኪዎች

እነዚህ ኩኪዎች ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ ወይም በድረ ገጻችን ላይ ወይም ከድረገጻችን ውጭ በይነመረብን እርስዎ በሚያስሱበት ጊዜ ከፍላጎትዎችዎ ጋር የተጣጣሙ መረጃዎችን ለእርስዎ ለመላክ እንድንችል ያገለግላሉ። የሚያዩትን ማስታወቂያ ብዛት ለመገደብ እና የማስታወቂያን ውጤታማነት ለመለካት ይጠቅማሉ። የእርስዎን መረጃ (ውሂብ) አንሸጥም ወይም ማንነትዎን አሳልፈን ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች አንሰጥም።

እነዚህን የማስታወቂያ ኩኪዎች አለመቀበል በድረገጻችን አጠቃቀም ላይ ምንም ተፅዕኖ አይፈጥርም። ይሁን እንጂ የማስታወቂያ ኩኪዎችን አለመቀበል በድረገጻችን ወይም በበይነመረብ ላይ ማስታወቂያዎችን ከመታየት አያስቆምም። ይህ የእርስዎን ፍላጎቶች ወይም ምርጫዎች የማያንጸባርቅ ማስታወቂያን ብቻ ያመጣል። እነዚህ ኩኪዎች በዋናነት በማስታወቂያ አስነጋሪ ድርጅቶች ፍላጎቶች ላይ የተመረኮዙ ናቸው። ማስታወቂያ አስነጋሪ ድርጅቶቹን ሙሉ ለሙሉ መዘርዘር አንችልም። ይሁን እንጂ ለማናቸውም የእርስዎን መረጃ (ውሂብ) አንሸጥም ወይም ማንነትዎን አሳልፈን ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች አንሰጥም።

የምናስቀምጣቸው ኩኪዎች ምሳሌዎች፦

_fbp: ተጠቃሚዎች በድረ-ገጹ ላይ ምን እንደሚፈልጉ በተሻለ ለመረዳት እና ለተጠቃሚው ተዛማጅ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ብቻ ለማሳየት በፌስቡክ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።

የማስታወቂያ ዒላማ አደራረግ

እንደ «እንደገና ማነጣጠር» (ከእኛ ድረ-ገጽ ውጪ በሚያስሱዋቸው ጣቢያዎች ላይ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ወይም በጣቢያችን ላይ ያሉ ምርቶችን ከተመለከቱ በኋላ የኢሜይል አድራሻን ማሳየት) የመሳሰሉ የላቀ ተጠቃሚን ዒላማ አድራጊ ባሕሪያትን መጠቀም እንደምንችል አስቀድመን እናሳውቅዎታለን። ከእርስዎ ፍላጎት ጋር በተሻለ ሁኔታ የተስማሙ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንዲቻል በጣቢያችን ላይ ካለው የቅርብ ጊዜ ባሕሪዎ ጋር በተያያዘ እነዚህ በኩኪዎች አጠቃቀም ሊከናወኑ የሚችሉ ተግባራት ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚወስኑት በአጋሮቻችን የቀረቡ ኩኪዎች ናቸው።
በአሳሽዎ ውስጥ የማስታወቂያ ኩኪዎችን አለመቀበል ወይም በአጋሮች በሚቀርቡት የማስታወቂያ ምርጫ አስተዳዳሪዎች ወይም በኢሜይሎች ውስጥ ከደንበኝነት ምዝገባ በመውጣት በማንኛውም ጊዜ በእርስዎ ላይ የሚደረግ የማስታወቂያ ማነጣጠር ተግባርን ማስቆም ይችላሉ።

የኩኪዎችን ማስቀመጫ እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?

ምርጫዎችዎ የመጨረሻ ምርጫዎች አይደሉም። በማንኛውም ጊዜ ከዚህ በታች በተገለጹት ዘዴዎች መሠረት ሁሉንም ወይም አንዳንድ ኩኪዎችን ማቆም ይችላሉ።

የአሳሽዎን ሶፍትዌር ማዘጋጀት

ለኩኪዎች አስተዳደር እና ምርጫዎች የእያንዳንዱ አሳሽ ውቅር የተለየ ነው። አሳሽዎን ኩኪዎችን እንዲከለክል ወይም እንዲቃወም በማዘጋጀት አንዳንድ የድረገጻችን ባሕሪያት ተደራሽ እንደማይሆኑ አስቀድመን እናሳውቅዎታለን። በዚህም በምንም ዓይነት መንገድ እኛ ተጠያቂ ልንሆን አንችልም።

ለኢንተርኔት ኤክስፕሎረር፦ http://windows.microsoft.com/fr-FR/windows-vista/Block-or-allow-cookies,

ለሳፋሪ፦ https://support.apple.com/kb/PH17191?locale=fr_FR&viewlocale=fr_FR,

ለክሮም፦ http://support.google.com/chrome/bin/answer.py?hl=fr&hlrm=en&answer=95647,

ለፋየርፎክስ፦ https://support.mozilla.org/en-US/kb/clear-cookies...

የእርስዎን ስማርት ስልክ ለማቀናበር

አይኦኤስ፦ https://support.apple.com/en-gb/HT201265,

አንድሮይድ፦ https://support.google.com/accounts/answer/32050?co=GENIE.Platform%3DAndroid&hl=en&oco=0,

የተመልካች ብዛት መለኪያ ኩኪን ማቀናበር

ለተመልካች ብዛት መለኪያ ሲባል በእርስዎ አሳሽ ላይ ኩኪዎችን የኛ ጣቢያ እንዲያስቀምጥ የማይፈልጉ ከሆነ በእርስዎ አሳሽ ላይ እንዲሰናከሉ የሚያደርጋቸውን ኩኪ እንዲቀመጥ የሚያደርገውን ከዚህ በታች ያለውን የማሰናኪያ አገናኝ ጠቅ ማድረግ ይችላሉ፦

ጉግል አናሊቲክስ፦ https://tools.google.com/dlpage/gaoptout?hl=en

የማስታወቂያ ክትትል ማድረጊያ ኩኪዎች አዘገጃጀት

በማስታወቂያ አስነጋሪዎች የቀረበውን የማስታወቂያ ክትትል ማድረጊያ ኩኪዎች ማስተዳደሪያ መድረኩን በመጎብኘት እና በውስጡ የቀረቡትን መመሪያዎች በመከተል የእነዚህን ኩኪዎች አጠቃቀም ሁኔታ ማስተዳደር ይችላሉ፦ http://www.youronlinechoices.com/fr/controler-ses-... በመሣሪያዎ ላይ ሊታዩ የሚችሉ የአሰሳ መረጃዎችን እና ማስታወቂያዎችን ለመወሰን እና እነዚህ ኩባንያዎች የሚጠቀሙባቸውን ኩኪዎች መቀበል ወይም አለመቀበል የሚችሉበትን ሁኔታ በዚህ መድረክ ላይ ከተመዘገቡት ኩባንያዎች አስቀድመው ማወቅ ይችላሉ።

ለትሬድላብ፦ http://tradelab.com/vie-privee-2/

ለአግዚዮም፦ http://www.acxiom.fr/a-propos-d-acxiom/information...

የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ኩኪዎችን ማቀናበር

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/help/568137493302217

ቲዊተር፦ https://support.twitter.com/articles/20171551-vos-...